ዓርብ 10 ኖቬምበር 2017

በ ኖቭ አለም አቀፍ አስጎብኚ ድርጅት ተዘጋጅቶ ለናንተ የቀረበ ............ስንቶቻችን ሀገራችን እናውቃታለን?................ ኢትዮጵያ ምን ዓይነት ሀገር ናት? 1. የቀዳማዊ የሰው ልጅ (የአዳም) መገኛ 2. የጥንታዊ ታሪክ ባለቤት (ከዞንዶ ንጉሥ እስከ ዛሬው መ/ት) 3. የጥንታዊ ሥልጣኔ ምንጭ (የአዱሊስ፣የሮሃ፣ የአክሱም፣….) 4. የጥንታዊ ሃይማኖት መገኛ (ህገ-ልቦና፣ ኦሪት፣… ) 5. በዓለም ለዘመናት ያልተቋረጠ በትረ-መንግሥት የነበራት (ከኖህ እስከ ቀ/ኃይለ ሥላሴ ንግሥና) 6. ባንድረዋ በቀስተ-ደመና መልክ በሰማያት የተገኘ– ንግርት 7. እነ ሆሜር ‹የቆንጃጅት ሀገር› ብለው በጥንት ታሪክ ያወደሷትና መሰከሩላት 8. ከ18 ያላነሱ ፈርኦኖችን ለምድረ ግብፅ ያበረከተች ሀገር 9. በዓባይ ሥልጣኔ ምንጭነት ምድረ-ግብፅ ድረስ ወርዳ ታሪካዊዎቹን ፒራምዶች እነ ሶፊንክስን በታሪክ ዓምድነት የተከለች ሀገር 10. በታሪክ መጀመሪያ የተመዘገበች ንግሥት (በሴት ንግሥት የተመራች) የተገኘችባት ሀገር 11. በዓለም ለመጀመሪያ የሥነ-ጽሑፍ ቋንቋ (ግእዝ) የተገኘባት ሀገር 12. ሳይንሳዊነቱ ተወዳዳሪያ የሌለው የምድሪቱ ቀዳማይ ፊደል ያላት 13. በዓለም ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአንድ ወጥ ድንጋይ ተፈልፍሎ የተሠራ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ያላት ( የቅ.ላሊበላ ውቅር አቤያተ ክርስቲያናት) ሀገር፣ 14. በዓለም ላይ የሚገኘው የአየር ጠባይ (ከውርጭ እስከ ከፍተኛ ሞቃታማ ሥፍራ) በሙሉ ተካቶ የሚገኝባት ብቸኛ ሀገር 15. ለሌላው ዓለም ያበረከተቻቸው እፅዋትና ተክሎች (ዝግባ፣ዋንዛ…)፣ እንስሳትና አራዊት (ዋልያ፣የሜዳ አህያ፣…)፣ እንደ ጤፍና ቡና ያሉ የተለዩ የተፈጥሮ ምርቶችን ያስገኘት 16. የግብርና ሥልጣኔ የተጀመረባት ሀገር፣ 17. የድሞክራሲ ሥርዓትን ለግሪኮች ያስተማረች (ቤተ-ሕዝብ፣ ቤተ-ምልክናና ቤተ-ክህነት ሦስቱ የሥልጣን ክፍፍል፤ እንዲሁም የገዳ ሥርዓት ዲሞክራሲያዊ አሠራር) 18. የተፈጥሮ ፀረ-ቫይረስ የሆኑትን እነ ቁንዶን፣ እነ በርበሬን፣ ሚጥምጣን፣ ከአፅራረ ትላትል (ኮሶ፣ መተሬ፣ እንቆቆ፣..)በምድሯ አፍርታ የምትገኝ ሀገር 19. የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን እምነት ፅንሠ-ሐሣብ ለዓለም ያስተዋወቀች ሀገር 20. የአምላክን ግማደ-መስቀል፣ ተከርኦተ-ርዕስ በቅርስነት የያዘች፤ ተቦተ ፅዮንን ይዛ በመጠበቅ የኖረች ሀገር 21. የቅዱሳን አስደናቂ ቃልኪዳን ያላት (ለምሳሌ በአቡነ አሮን ቃልኪዳን ከአናቱ ባዶ ሆኖ ዝናብ የማያፈሰው የቤተ-ክርስቲያን ጣራና የዝንጆሮዎች አዝመራ አለመብላት ቃል ኪዳን ያለባት ሀገር… 22. በቅኝ ገዥዎች ያልተንበረከከች ሀገር፣ ነጭ ሕዝብን በማሸነፍ የጥቁርን አሸናፊነት ያሣየችና ነጮችን ያሳፈረች ሀገር፣ የነፃነት ተምሳሌት የሆነች ሀገር 23. የተባበሩት መንግሥታን ለመመሥረት ከአፍሪካ ሀገሮች አንዷና ብቸኛዋ የመጀመሪያ ሀገር፤ የአፍሪካ አንድነትን መሥራችና መቀመጫ ሀገር 24. በልዩ ልዩ አስደናቂ ጥበባት የሠለጠኑ ልጆች ያሏት ልመሳሌ ሌባ ሻይ፣ መፍትሔ-ሥራይ፣ ምላ-ሃብት፣…ታምር የሚሠሩት እነ መተት፣…. 25. እንግዶችን በክብር በመቀበል ፍትሕን፣ እንግዳ ተቀባይነትን፣ ሃይማኖትኝነትን፣…መመሪያዋ መሆኑን ያስመሰከረች ሀገር፣ 26. መጤ ሃይማኖትን በየዋህነት የተቀበለች የስደተኞች መጠጊያ ሀገር 27. በሌሎች የዓለም አቤያተ ክርስቲያናት ያልተገኙ እንደ ኩፋሌ፣ ሄኖክ፣ ዮሴፍ ወልደኮሪዮስ፣… የብሉያት ቀደምት መጻሕፍት የሚገኙባት ሀገር 28. ዘመናዊ ህክምና ያልደረሰባቸውን በሽታዎች የሚፈውስ የፀበል ፀጋን የታደለች ሀገር 29. የመንፈስ አዛጦን የታደለች፡- የሥነ ነፍስን÷ የሀብተ መንፈስን (ሥነ-ልቦና)÷ የሥነ-ምግባር ሰናያት (ትዕግሥት፣ ትህትና፣ አፍቅሮ ሰብዕ፣ ንፅሐ-ኅሊና…) ÷ የምድሪቱ መልካም ባህላዊ እሴቶች (ጉድፈቻ፣ ማደጎ ልጅ፣ የነፍስ ልጅ…) በአንጀል ሚሮ:: www.novtravelt.blogspot.com
















ቅዳሜ 21 ኦክቶበር 2017

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ከኢትዮጵያ የዱር እንስሳትና ተፈጥሮ ታሪክ ማህበር በጋራ የአለም አቀፍ የስደተኛ አእዋፍ ቀን በሻላ፣ ጭቱ እና ዝዋይ ሀይቅ ዙሪያ በመገኘት ሀይቆቹ ላይ በተጋረጠባቸው ከፍተኛ አደጋ ላይና መፍትሄዎቹ ምንድን ናቸው በሚል ዙሪያ ውይይት በማድረግ አከበሩ፡፡

ከታዩት ችግሮች መካከል፤ የሀይቆቹ ውሃ መቀነስና ብክለት እየተባባሰ መሄድን ተከትሎ እየተከሰተ ያለው ተጓዳኝ ችግር ዋነኛው ነበር፡፡
በፕሮግራሙ ላይ ዊት ላንድስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ፣ ብዝሀ-ህይወት ኢንስትቲዩት፣ ደንና አካባቢ ጥበቃ ሚንስቴር፣ ኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳትና ደን ኢንተርፕራይዝ እና የዘርፉ ተመራማሪዎች ተገኝተዋል፤ ውይይቱም ላይ ሀሳባቸውን አቅርበዋል፡፡
የዝዋይ ሃይቅ ከጊዜ ወደ ጊዜ ውሀ መጠኑ መቀነሱ በዙሪያው ውሀውን የሚጠቀሙ ድርጅቶችና ግለሰቦች አግባብነት በጎደለው መልኩ መጠቀማቸው ምክንያት ሆኗል፡፡
ከዚህ ሀይቅም በመነሳት ወደ ሻላ ሀይቅ በመሄድ ይገብር የነበረው ቡልቡላ ወንዝ ሙሉ በሙሉ ጉዞው ተገትቶ ቆሟል፤ ስለሆነም በአቢጃታ ላይ የተከሰተው ከፍተኛ ችግር በሻላም ላይ በቅርቡ እንደሚከሰት አመላካች ሁኔታዎች ታይተዋል፡፡
በቅርቡም በሻላ ሀይቅ ላይ ሊገነባ የታሰበው የሶዳ አሽ ፋብሪካ በርጋታ ሊጤን የሚገባው እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡
ለእነዚህና ሌሎች ችግሮች ባለሙያዎቹ በመፍትሄነት ያቀረቧቸው ሀሳቦች የውሀ አጠቃቀሙ ሁለቱንም በማይጎዳ መልኩ እንዲሄድ በጋራ ስራዎችን መስራት፣ ውሀውን በከፍተኛ ደረጃ የሚጠቀሙ ድርጅቶች ተገቢውን ክፍያ በመክፈል እንዲጠቀሙና ይህም ሀይቆቹን ለመጠበቅ ለሚሰሩ ስራዎች አጋዥ እንዲሆን ማስቻል ፣የሀይቆቹን ዙሪያ ከበካይ ፍሳሽና ደረቅ ቆሻሻዎች መጠበቅ እና ጠብቆ በማልማት ይዞታቸው እንዲመለስ መስራት ሲሆን ይህ ሳይሆን አሁን እየተካሄደ ባለው መልኩ ያልተገባ አጠቃቀም ከቀጠለ ሀይቆቹ በቅርቡ ላለመጥፋታቸው ምንም ዋስትና እንደማይኖር የሚሉት የውይይቱ ሀሳቦች ነበሩ፡፡
ግንቦት 14/2009 /የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን / by anjel miro